ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

የካቲት 15/2014 (ዋልታ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ሞሀመድ አሕመድ አል ቦዋርዲ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በምስራቅ አፍሪካና በባሕረ-ሰላጤው ስላለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ መምከራቸውን የኢቢሲ መረጃ አመላክቷል።

ሁለቱ አገራት በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ በጋራ በሚሰሩበትና ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ዙሪያም ተወያይተዋል።