ኢትዮጵያና ጀርመን  በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካቲያ ኬውል ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ጀርመንን ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቁመው፤ ግጭቱን አስመልክቶ በቅርቡ ይፋ የተደረገው ሪፖርት ፖለቲካዊ ፍላጎት ያለውና ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ሁለቱ ሀገራት በኢነርጂ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።