ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን ሀይል ለመደምሰስ በጥሩ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ  በማይጠብሪ ግንባር የሚገኘው ሠራዊት ገለፀ

በማይጠብሪ ግንባር የሚገኘው ሠራዊት

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን ሀይል ለመደምሰስ በጥሩ የስነልቦና፣ የሞራል እና የትጥቅ  ዝግጅት ላይ  እንደሚገኝ  በማይጠብሪ ግንባር የሚገኘው ሠራዊት ገለፀ።

በእስካሁኑ የግንባሩ የጦር ሜዳ ቆይታ ጠላትን በማጥቃትና በመከላከል ረገድ እየተመዘገበ  ያለው ድል አመርቂ እንደሆነ የገለጹት የግንባሩ ሠራዊት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሠለፉበትን አላማ  በድል ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ጀግኖች አባቶች ያቆዩልንን የሃገር አንድነት በአጥንትና በደማችን እናስቀጥላለን የሚሉት  የሠራዊቱ አባላት፣ በቅርቡ ድልን እንቀዳጃለን ብለዋል።

በግንባሩ የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሻም ከሰራዊቱ ጋር እንደተሰለፉና በቅርቡም የኦሮሚያ ልዩ  ሀይል ግንባሩን እንደተቀላቀሉ የግንባሩ አመራሮች ገልጸዋል።

(በታሪኳ መንግስተአብ)