ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በአምስት ሺህ የሴቶች የፍጻሜ ውድድር በሶስተኛነት አጠናቀቀች

ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያዊቷ አትሌት  ጉዳፍ ጸጋይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በአምስት ሺህ የሴቶች የፍጻሜ ውድድር በሶስተኛነት አጠናቀቀች፡፡

በዚህም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ሶስተኛ በመውጣት ለሀገሯ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 5ኛ፣ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ደግሞ 6ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቅቀዋል።