ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቋሚነት ወገኖቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን

ታኅሣሥ 23/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቀጣይነት ባለው መልኩ ከእናት አገራቸው ኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ እና በቋሚነት ወገኖቻቸውን እንዲደግፉ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ጥሪ አቀረቡ፡፡

በስዊድን፣ ፖላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚሸፍናቸው በስዊድን፣ ፖላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ እና ፊንላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በ”ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ” ማኅበር አስተባባሪነት በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይና የተጎዱ ወገኖችን በቀጣይነት ለመደገፍ የሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በጀርመን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ለሀገራዊ ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የውይይት መድረኩን ያስተባበሩትን በማመስገን በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።