ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን ኅልውና የሚፈታተን ፖሊሲ ለመጫን እያደረገች ያለውን ጥረት ለማውገዝ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በርከት ያሉ እውነታዎች ተገልጠዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን አንድ በመሆን ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባዊያንን አውግዘዋል፡፡
ተቃውሞው በአሜሪካ እና በአውሮፓ ከ27 በላይ ከተሞችን አጥለቅልቋል፡፡
በእንግሊዝ ብቻ 50 ሺሕ የሰልፉ ተሳታፊዎች የለንደንን ጎዳና በተቃውሞ ሰልፍ ንጠዋል።
“በቃ” #NoMore የሚል መፈክር በመላው ዓለም ሲስተጋባ ውሎ አድሯል፡፡
ሌሎች አፍሪካዊያንም ከሁሉም የአኅጉሪቱ ማዕዘናት ወደ #Nomore እንቅስቃሴ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ትግሉ ከኒዮኮሎኒያሊሲም (አዲሱ ቅኝ ግዛት እሳቤ) ጋር የሚደረግ የአፍሪካዊያንን ነጻነት ማረጋገጫ መሆኑን አሳይቷል፡፡
‹‹#NoMore ከአሁን በኋላ ኒዮኮሎኒያሊዝም የለም፤ኢምፔሪያሊዝም ይብቃ!፤የአንዳንድ ምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት ይብቃ!›› የሚሉት መፈክሮች በየከተሞቹ ከተሰሙት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡