ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ
 
ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዳያስፖራዎች እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓልን በጎንደር እንዲያከብሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ጥሪ አቀረቡ።
 
ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በጎንደር ከተማ የጥምቀትን በዓልን ለማክበር ሁሉም ከውጭ የሚገቡም ሆኑ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪ ማቅረቧን አስረድተዋል።
 
ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የተጎዱ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በበኩላቸው በጥምቀት በዓል ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የተካተቱበት የባሕል ሳምንት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
 
በጥምቀት በዓል የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹሩባ) በክብር ወደ ጎንደር ከተማ የሚገባ መሆኑን ከንቲባው ገልጸው ይህንን ታሪካዊ ኹነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጎንደር በመገኘት መታደም እንደሚገባቸው መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!