ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጣሊያን በተካሄደ የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፉ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጣሊያን አገር ካምፓሲዮ በተካሄደው አመታዊ የአገር አቋራጭ ውድድር አሸንፈዋል።
በሴቶች በተደረገው የ6 ኪሎሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት ጸሃይ ገመቹ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አሸንፋለች።
በዚሁ ውድድር ላይ የተካፈለችው ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጽጌ ሃይለስላሴ ሶስተኛ ደረጃ አግኝታለች።
በአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድሩ ኬንያዊቷ ሊሊያን ሬንጌሩክ ከጸሃይ ገመቹ በመቀጠል ሁለተኛ ወጥታለች።
በሌላ በኩል በወንዶች በተካሄደው የ10 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ንብረት መልዓክ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪምሊሞ የ10 ኪሎሜትሩ ውድድር አሸናፊ ሲሆን፣ ሌላኛው ዩጋንዳዊ ኦስካር ቼሊሞ ሶስተኛ መውጣቱን የአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡