ኢትዮጵያ ሙስናን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ደረጃዋን አሻሻለች

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየዓመቱ በሚያወጣው የዓለም አቀፍ የአገሮች የሙስና ደረጃ ኢትዮጵያ 2 ደረጃዎች በማሻሻል ከ180 አገሮች መካከል 94ኛዋ ሆነች።

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2020 የሙስና አመለካከት መረጃውን ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንደመላከተው ኢትዮዽያ ከ180 አገሮች ከመቶው በተሰጠ ነጥብ 38 በማስመዝገብ 94ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የመጨረሻውን ደረጃ እንደያዙ ሪፖርቱ አመልክቷል።

ዴንማርክ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፊንላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ስዊድን እና ስዊዘርላንድ ብዙም ሙስና ችግር ያልሆነባቸው አገሮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ሪፖርቱ የሚያሳየው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ቀውሶችን የያዘ ስለነበረ በአገሮች ሙስና በጣም የተስፋፋ መሆኑን ነው፡፡

መረጃው አንዳንድ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም አብዛኞቹ አገሮች ሙስናን በብቃት ለመወጣት አለመቻላቸውን ያመለክታል።