ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናድ ከአፍሪካ ሃገራት በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ

ሚያዚያ 13/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ 844 ሺሕ 589 የተመዘገቡ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ተቀብላ

በማስተናድ ከአፍሪካ ሃገራት በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከእነዚህ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መካከል ደቡብ ሱዳናዊያን፣ ሱማሊያዊያን እና ኤርትራዊያን ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙም ተጠቁሟል፡፡

34 ሺሕ 485 ስደተኞች የኮቪድ ክትባት የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 30 ሺሕ 65ቱ የተሟላ የክትባት ሂደትን ጨርሰዋል፡፡