ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ሊቀመንበርነትን ተረከበች

ሙፈሪሃት ካሚል

ማጋቢት 24/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ሊቀመንበርነትን መረከቧን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

አስራ አንድ የምስራቅና አፍሪካ ቀንድ ሀአራት የሚሳተፉበት ቀጣናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ላለፉት ስድስት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ እንደቆየ ተናግረዋል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ኬንያ የሚኒስትሮች ፎረሙን ስትመራ ቆይታለች ብለዋል፡፡

የኬንያ መንግሥት ላደረገው ደማቅ አቀባበል፣ ቆይታችን የተሳካ እንዲሆን ለነበረው ዝግጅት እንዲሁም ፎረሙን በመምራት ለተጫወተው የመሪነት ሚና ምስጋናቸውን ያቀረቡት ሚኒስትሯ በተለይም ለኬንያ የሰራተኞች ሚኒስትር ስሞን ቼሉጉዊ የከበረ ምስጋናቸውን በማኅበራዊ ትስሰር ገጻቸው አቅርበዋል::

በቀጣናው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በኢትዮጵያ የመሪነት ዘመን ውጤታማ ሥራዎች እንደሚከናወኑ የቀጣናው አባል አገራት በኢትዮጵያ የመሪነት ወቅት የላቁ ተግባራት እንደሚከናወኑ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልጸው እኛም የተጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት በቁርጠኝነትና በታታሪነት እንሰራለን ብለዋል::

ለዚህ ዝግጅት ስኬት ተባባሪ የሆነውን ዓለ ዐቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በተለይም የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ዳይሬክተር መሀመድ አልከይር እስከአሁን ላደረጉት ድጋፍና በቀጣይም ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW