ኢትዮጵያ በዓመት ማምረት ከምትችለው 94 ሺሕ ቶን አሳ 60 ሺሕ ቶን ብቻ እያመረተች ነው ተባለ

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ በዓመት 94 ሺሕ ቶን አሳን የማምረት አቅም ቢኖራትም የምታመርተው ግን 60 ሺሕ ቶን ብቻ መሆኑ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የአሳ ሀብት አጠቃቀምን በሚመለከት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

የአሳ ምርትን በሀይቆች ላይ በስፋት ማምረት ቢቻልም በግድቦችና ወንዞች ላይ በበቂ ሁኔታ እየተመረተባቸው አይደለም ተብሏል።

ኢትዮጵያ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2014 እስከ 2018 ከውጭ የተለያዩ የአሳ ምርቶችን ለማስገባት 77 ሚሊየን ብር አውጥታለች ነው የተባለው።

አሳ ለማምረት አስፈላጊው ግብዓትና እውቀት ቢኖርም እየተጠቀምንበት አይደለም ተብሏል።

የአሳ ምርትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም ሆነ ወደ ውጭ በመላክ ሀገሪቱ ማግኘት ያላባትን ገቢ እንድታገኝ በፖሊሲ ደረጃ የተደገፈ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመላክቷል።

በትዕግስት ዘላለም

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW