ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2050 የካርበን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ግብ አስቀምጣ እየሰራች ነው -ጠ/ሚ ዐቢይ

ጥር 8/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2050 የካርበን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ግብ አስቀምጣ በትኩረት እየሰራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በሚመክረው15ኛው የአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ “ሰስቴኔቢሊቲ” ጉባዔ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እያከናወነች መሆኑን አብራርተዋል፡፡