ኢትዮጵያ ብሪክስን ተቀላቀለች

ነሔሴ 18/2015 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ተገለጸ፡፡

የብሪክስ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን እና አርጀንቲና የብሪክስ አባል እንዲሆኑ ውሳኔ አሳልፏል።

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው ጉባዔ ሀገራቱ በፈረንጆቹ ከጥር 2024 ጀምሮ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆን ይችላሉ ተብሏል።

ብሪክስ የብራዚል፣ የሩሲያ፣ የሕንድ፣ የቻይና እና የደቡብ አፍሪካ ጥምረት መሆኑ ይታወሳል፡፡