ሰኔ 24/2013(ዋልታ) – የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በትግራይ ክልል ተግባራዊ ያደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ በክልሉ ላይ ለውጥ ለማምጣት ተስፋ ሰጪ እርምጃ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ በሰጡት ወርሃዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ እያደረገ ላለው ከፍተኛ መጠን ላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እውቅና ሊሰጠው ይገባል።
ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትም ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉበት መንገድ ሊመቻቻልቸው እንደሚገባ አምባሳደሩ በዚሁ መግለጫቸው ላይ ማስታወቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡