ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብሩንዲውን ፎፊላ ፒኤፍ 5 ለ1 አሸነፈ

ነሐሴ 12/2014 (ዋልታ) በሴካፋ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ቡድን የቡርንዲውን ቡድን ፎፊላን በሰፊ የግብ ልዩነት ረተዋል።

ዛሬ 10:00 ሰዓት በጀመረው የሁለተኛ ዙር ጨዋታ ንግድ ባንኮች የብሩንዲ አቻውን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

በጨዋታው ልማደኛዋ አጥቂ ሎዛ አበራ ሶስት ግቦችን አስቆጥራ ሀትሪክ ስትሠራ መዲና አዎል እና ናርዶስ ጌትነት ደግሞ አንድ አንድ ግብ አስቆጥረዋል።

መዲና አዎል በሴካፋ ውድድር አምስት ጎሎች እና ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችታ ስታቀብል ፤ ሎዛ አበራ ደግሞ በሁለት ጨዋታ ስምንት ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራች ትገኛለች።

በሙባረክ ፈንታ