ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ሁለት የድጋፍ ስምምነቶችን በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱ ካማራ ተፈራርመውታል፡፡

የተደረገው አጠቃላይ የድጋፍ ስምምነትም 118  ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ወይም 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡