ኢትዮጵያ ከነባር ችግሮቿ ተላቅቃ በተስፋዋ ጎዳና እንድትገሠግሥ እየታገልን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 19/2014 (ዋልታ) “ኢትዮጵያ ከነባር ችግሮቿ ተላቅቃ በተስፋዋ ጎዳና እንድትገሠግሥ እየታገልን ነው ያለፈው ችግሯ ውርስ መከራችንን ሊያረዝመው ይታገለናል። እኛ ደግሞ ተስፋችንን ለማለምለም እንታገላለን።በችግራችን ከተዋጥን ይነግሥብናል። ለተስፋችን ከታገልን እንነግሥበታለን”ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በዚህ እሑድ ሁላችንም መቻቻልና አብሮነት እንዲያሸንፍ እንጸልይ። ነጋችን ብሩህ እንዲሆን ደግሞ ወጥተን ዛፎችን እንትከል። ተሸናፊው ውርስ ችግር ሊያሳምመን እንጂ ሊያሸንፈን አይችልም” ብለዋል።