ሚያዚያ 19/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ስምምነትን መፈረሟን አስታወቀች።
ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአፍሪካ ህብረት በመገኘት የፈረሙ ሲሆን
ኢትዮጵያ የኤጀንሲው አባል መሆኗ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
ይህ ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው የጤና ዘርፍ መሻሻል እና የህዝብ የጤና ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲህ አይነቶቹ አህጉር አቀፍ ተቋማት መመስረታቸው ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር ዶ/ር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ፣ የተመጣጠነ የመድኃኒት አቅርቦት እና የቁሳቁስ እቃዎች ስርጭት በአፍሪካ አስተማማኝ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባም መገኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።