ኢትዮጵያ የወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች መሆኗ ተገለጸ

ሁሪያ አሊ

ታኅሣሥ 1/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች መሆኗን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በፖላንድ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ላይ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ የአፍሪካ አህጉር ከ60 በመቶ በላይ ወጣቶች የሚኖሩበት እንደመሆኑ ይህንን መልካም እድል መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች የኢንተርኔት ግንኙነትን ወደ እውቀት፣ ፈጠራ እና የስራ እድል ሊቀይሩት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በኢትዮያ ከ15 እስከ 29 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 25 ሚሊየን በላይ ካሉ ወጣቶች በየአመቱ ከ3መቶ ሺሕ በላይ  ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይመረቃሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ኢትዮጵያ በዘርፉ ወደ ፊት ለመራመድ እንዲያስችላት እየሰራች ያለችውን የማሻሻያ ስራዎች ለፎረሙ ማብራራታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።