ኢትዮጵያ የ2022ቱን ዓለም ዐቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤን ልታስተናግድ ነው

በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

መጋቢት 8/2014 (ዋልታ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን እና ኤክስቴሽያ አዘጋጅነት ኢትዮጵያ የ2022ቱን “ዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤን” ልታስተናግድ መሆኗ ተገለጸ፡፡

በጉባኤው ከ30 በላይ አገራት የተውጣጡ ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ ሚኒስትሮች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኃላፊዎች እና ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የኢኖቬሽን ዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መደረጉ ኢትዮጵያ ተመራጭ እየሆነች መምጣቷን ማሳያ ነው ብለዋል።

ጉባኤውን ለማስተናገድ የኢትዮጵያን ዝግጁነት ያረጋገጡት ሚኒስትሩ ጉባኤው ኢትዮጵያ ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አጋዥ የሆኑ የመፍትሄ ሃሳቦችን የምታገኝበት እንደሚሆንም ተናግረዋል።

ጉባኤው ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ለፖሊሲ አውጪዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የዲጂታል ቴክኖሎጂ የመፍትሄ ሃሳቦች የሚቀርቡበት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW