መጋቢት 13/2014 (ዋልታ) ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሥራ ዕድል ፈጠራና ውጭ ምንዛሬ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጡ መንግሥት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ የለቡ ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ፓርኮቹ ምን አይነት ችግሮች እየገጠማቸው ነው፤ እንዴት ሊፈታ ይችላል፤ ከመንግሥት ምን ይጠበቃል? የሚለው እየተለየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማም ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ከንቲባዋ አብራርተዋል::
በጉብኝቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የየከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡