ኢዜማ የምርጫ ማኒፌስቶን ይፋ አደረገ

መጋቢት 14/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የምርጫ 2013 ማኒፌስቶ ወይም የምርጫ ቃልኪዳን ስነድ ይፋ አደረገ።

ፓርቲው ለጋዜጠኞች በስጠው መግለጫ ዜጎች ቢመርጡት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚያሳካቸውን እና የሚመራባቸውን መስረታዊ ሃሳቦች አስታውቋል።

የኢዜማ የምርጫ 2013 ማኒፌስቶ ሰምንት ክፍሎች የያዘ ሲሆን፣ የፓርውን መለያ፣ የሀገር ደህንነት ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች፣ የፖለቲካ መሰረታዊ ችግሮችና አማራጭ  የመፍትሄ ሀሳቦች፣ የኢኮኖሚ፣ የውጪ ግንኙነትና የማህበራዊ ችግሮችና መፍትሄዎች እንዲሁም ስትራቴጂና  ፋይናንስ ላይ ትኩረት ማድረጉን አስታዉቋል።

(በህይወት አክሊሉ)