የካቲት 12/2013 (ዋልታ)- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፓርቲውን የምርጫ ምልክትና መሪ ቃል ይፋ አደረገ፡፡
የፓርቲው የምርጫ ምልክት ሚዛን ሲሆን ይህም ሁሉንም ዜጋ በእኩል የሚያይ የፍትህ መርህን ያነገበ ነው ተብሏል፡፡
እኩልነት፣ ኢ-አድሎአዊነት፣ ፍትህና ስምምነት ደግሞ የምልክቱ ትንታኔ ወይም መገለጫዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
ኢዜማ በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ለፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች መሪ ቃሉን ይፋ አድርጓል፡፡
“ንቁ ዜጋ፣ ምቹ አገር” የፓርቲው መሪ ቃል ሆኖ ይፋ የተደረገ ሲሆን የዜጎችን ተሳትፎና የሚገቡትን ቃልኪዳን አጠቃሎ የሚናገር መሆኑ ተገልጿል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)