ኢጋድ 2 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ለኮቪድ መከላከያ የሚውሉ ቁሳቁስ ለጅቡቲ አበረከተ

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ለኮቪድ መከላከያ የሚውል ቁሳቁስ ለጅቡቲ አበረከተ፡፡

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኢጋድ አምቡላንስን ጨምሮ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጅቡቲ ድጋፍ ማድረጉን በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በኢጋድ አባል ሃገራት መካከል ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግም ነው ያስታወቁት፡፡

አክለውም በወረርሽኙ የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን በሚደረገው ጥረት የኢጋድና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ገልጸዋል፡፡