ኤርትራ የተመድ የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን ለማገልገል በድጋሚ ተመረጠች

ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን ከፈረንጆቹ 2022 እስከ 2024 ለማገልገል በድጋሚ በመመረጧ የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ክብርና ደስታ እንደተሰማው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የኤርትራን የምክር ቤቱ አባል ሆና እንድትመረጥ የአፍሪካ ህብረት መደገፉን የገለጸው መግለጫው፣ በአዲሱ ምርጫ መሰረት ኤርትራ በጄኔቫ መቀመጫውን ባደረገው ምክር ቤት ለሶስት ዓመታት ያህል ታገለግላለች ብሏል፡፡
መግለጫው ኤርትራ ለዜጎች መብት ታትራ እየሰራች መሆኑንና በዚህም በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና ምርታማነት፣ በድህነት ቅነሳና በመሰረተ ልማት ግንባታ መሻሻሎች መታየታቸውን ጠቅሷል፡፡
የኤርትራ መንግስት የሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ፈርማለች፤ ለየሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን ፈርማለች፡፡
የመንግሥታቱ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት አሜሪካን፣ አርጀንቲናን፣ ቤኒንን፣ ካሜሮንን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስን፣ ጋምቢያንና ህንድን ጨምሮ 18 ሀገራትን የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት አባል አድርጎ መርጧል፡፡