ኤኮን የ #በቃ #NoMore ንቅናቄን ተቀላቀለ

ኅዳር 20/ 2014 (ዋልታ) አፍሪካ አሜሪካዊው የሙዚቃ አቀንቃኝ ኤኮን የ #በቃ #NoMore ንቅናቄን ተቀላቀለ፡፡
ከምዕራባውያን የሚሰነዘሩ ጫናዎችን ለመቋቋም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ አርቲስቶች እና የተለያዩ ባለሙያዎች የ #NoMore ዘመቻውን ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡
ዝነኛው የሙዚቃ አቀንቃኝ ኤኮን ዓለምን እያነቃነቀ ያለውን የ #NoMore) ንቅናቄ በመደገፍ እንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ አለፍ ሲልም በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና ተቃውሟል፡፡
አርቲስቱ በኢንስታግራም ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ነው ንቅናቄውን የተቀላቀለው፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!