ኤጀንሲው የትራፊክ ፍሰትን የሚያሻሽሉ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገለጸ

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸ፡፡

ወቅቱ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የሚያስተምሩበት ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ኤጀንሲው ተለዋዋጭ የትራፊክ ፍሰት ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ የትራፊክ መጨናነቅን በተለየ ሁኔታ ፍሰቱን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤልያስ ዘርጋ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ የፍሰት መጨናነቅ ችግሮች እንዲፈቱ ከትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ ተደርሷል ማለታቸው ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች መግቢያና መውጫ በሮች የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት በማያውክ መልኩ እንዲስተካከሉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች አካባቢ ኤጀንሲው እያደረጋቸው ከሚገኙ የማሻሻያ ስራዎች ምልክትና ማመላከቻዎች መትከል፣ አሽከርካሪዎች አካባቢው ላይ ባሉ አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ በማድረግ ከዋናው መንገድ ገባ ባሉ ስፍራዎች ተሳፋሪዎቻቸውን እንዲጭኑና እንዲያወርዱ የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን የማሸጋሸግና ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW