እርዳታ ተከለከልኩ የሚለው አሸባሪ ድርጅት የእርዳታ እህል የተከማቸባቸውን መጋዘኖች አቃጥሏል

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በመተው በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ህወሓት በአንድ በኩል እርዳታ እንዳይደርስ ተከለከልኩ በማለት ይጮሃል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የእርዳታ እህል የተከማቸባቸውን መጋዘኖች ማቃጠሉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

አሸባሪው ሰሞኑን በአፋር ክልል የነበረንና የእርዳታ እህል የተከማቸበትን መጋዘን አቃጥሏል።
የዚህ አሸባሪ ቡድን ዓላማ ግልጽ ነው፤ በትግራይ ህዝብ ስም የራሱን የኖረ ጥቅም ማስከበር ነው ተብሏለል።
መንግስት የማሰቢያ ጊዜ የሰጠው የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በአሸባሪው ድርጅት አመራሮችና ካድሬዎች ተማሯል፤ በየከተሞች ህዝቡ ጥያቄ እያነሳ ይገኛል። ልጆቻችንስ ማለትም ጀምሯል።
የአሸባሪው አመራሮች ደግሞ ልጁን ያልሰጠ እርዳታ አያገኝም በሚል ከህዝቡ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል።
ይህ ቡድን ህጻናትን ሳይቀር ወደ ጦርነቱ እየማገደ ሲሆን፤ በቅርቡም በአፋር ክልል ሶስት ብርጌድ ታጣቂዎቹ መደምሰሳቸው ይታወሳል።