እቅዶችን በዲጂታል መንገድ መከታተልና መገምገም ግልጽነትንና ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ ያስችላል – ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

                         የብሔራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 05/2013 (ዋልታ) – እቅዶቻችንን በዲጂታል መንገድ ክትትልና ግምገማ ማድረግ ግልጽነትንና ፍትሃዊነትን ማርጋገጥ ያስችላል ሲሉ የብሔራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

የኮሚሽኑ በአስር አመታት የልማት እቅድ ክትትልና ግምገማ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ የሚል ራዕይ ያለውን የአስር አመቱ መሪ የልማት አቅድ እውን አንዲሆን ተቋማት ዕቅዶቻቸውን በመናበብ፣ በግልጽነትና በቅንጅት መተግበርና መገምገም ሊኖርባቸው እንደሚገባም ኮሚሽነር ፍጹም ገልጸዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፣ ባለፉት አመታት አቅዶችን የመተግበር ክፍተት እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን የኅብረተሰቡን ጥያቅ በሚመልስ ልክ አዘጋጅቶ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የልማት እቅዱ ወደ ብልጽግና ማማ የምንጎዝበት መንገድ በመሆኑ እቅዱ የሚተገበርበት ሥስርአት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።

በዚህም ሁሉም ተቋማት የራሳቸውን ባህርይ በሚናበብ መልኩ እቅዱን መተግበርና መገምገም ተገቢ እንደሆነም አመልክተዋል።

የልማት እቅዱ 10 የልማት ትኩረት ምሳሌዎች ያሉት ሲሆን ማክሮ ኢኮኖሚ፣ ኢኮኖሚ፣ መሰረተልማት፣ ማህበራዊ ልማት፣ ፍትህ እና የህዝብ አገልግሎት እንዲሁም አካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ የሚሉ ስድስት ዘርፎች እንዳሉት ተገልጿል።

(በትዝታ መንግስቱ)