‹‹እኛ መንግሥታችንን መርጠናል›› ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) ‹‹እኛ ከ100 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን መንግሥታችንን መርጠናል›› ሲሉ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የኅዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ‹መንግሥትና አገር እናፈርሳለን› ብለው ለሚቃዡ አካላት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
በመስቀል አደባባይ አሸባሪዎቹን ሕወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሰራዊትን እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ ኃይሎችን የሚደግፈውን ሕዝባዊ ሰልፍ ጠቅሰው በቲውተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይህን ያሉት፡፡
‹‹እኛ ከ100 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን መንግሥታችንን መርጠናል›› ያሉት ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሚኒስትሩ ስለሺ (ዶ/ር) አምባገነን ጨቋኞችን አይቻልም ስንል በአንድነት ቆመናል ብለዋል፡፡
በሰላምና የመኖርና የመልማት መብት አለን ሲሉም አክለዋል፡፡
ለእኩልነት፣ ፍትሕና ነፃነት ራሳችንን አሳልፈን እንሰጣለንም ሲሉ አስምረዋል፡፡
ሚሊዮኖች በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እና ሌሎችም ከተሞች እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ ብለዋል ሲሉ የጻፉት አማካሪ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ብለዋል፡፡