ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 385 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 385 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት  572 ሴቶችንና 112  ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 385 ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።