ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 6 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 6 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህ መሰረት በትናንትናው ዕለት 633 ሴቶችንና 248 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 6 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።