ከሳዑዲ አረቢያ 455 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

ነሀሴ 21/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 129 ህጻናት እና 326 ሴቶች በአጠቃላይ 455 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።