ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ስልጠና እየወሰዱ ነው

የካቲት 29/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ተቋም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ለተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በሥልጠናው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ እና ሶማሊያ የተውጣጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተሳተፉ ነው።

ከጃፓንና ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በመተባበር የሚሰጠው ስልጠና በቀጣናው አገራት የሚፈጠሩ የሠላም መደፍረስ ችግሮችን ለማስቆም ያግዛል ነው የተባለው፡፡

ጦርነት በሠው ልጆች ላይ የሚያስከትለው መዘዝ ከፍተኛ በመሆኑ ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከልና ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ከሁሉም ተባባሪ አገራት ጋር እየተሠራ መሆኑን የዓለም ዐቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሰብስቤ ዱባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት አንዷ መሥራች አገርና በኅብረቱም ብዙ ቁጥር ያለው ጦሯን ለሠላም ማስከበር ተልዕኮ እየላከች ያለች አገር መሆኗን የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ናቸው፡፡

የዓለም ዐቀፍ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ትምህር ቤት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጌቱ ታዬ በበኩላቸው ሠልጣኞች የተባበሩት መንግሥታትን ተልዕኮ ተቀብለው ከመሠማራታቸው በፊት ስለ ግጭት መከላከል ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!