ከተማ አስተዳደሩ ለ91 ማኅበራት የመሥሪያ ሼዶችን አስረከበ

ሚያዝያ 15/2014 (ዋልታ) የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ 456 ወጣቶች እና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ለ91 ማኅበራት የመሥሪያ ሼዶችን አስረከቡ።

ከንቲባዋ በክፍለ ከተማዋ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችም የታደሱ ቤቶችን አስረክበዋል።

በተጨማሪም ከንቲባዋ አበበች ጎበና የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል በመገኘት ለወለዱ እናቶች እና ልጆቻቸው የበዓል ስጦታ አልባሳትን ሰጥተዋል፡፡ ለሆስፒታሉም የበሬ ስጦታ አበርክተዋል።

 

በሜሮን መስፍን