ከተማ አስተዳደሩ ለ99 የተሰው ዘማች ቤተሰቦች የቤትና ለ1 ሺሕ 450 ቤተሰቦች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚገኙ ከ1ሺሕ 450 በላይ የዘማች ቤተሰቦች ለልደት በዓል መዋያ እንዲሆን ለእያንዳንዳቸው የበግ፣ ዶሮ፣ ዘይት፣ ዱቄትና ስኳር ስጦታ አበረከተ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ዘማች ቤተሰቦቻቸው ለተሰው 99 ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት አስረክቧል።

በተጨማሪም ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው የመጡ ዲያስፖራዎች ለዘማች ቤተሰቦች እንዲሆን  ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡

ስጦታውን ለዘማች ቤተሰቦች ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ለሀገር ክብር ሲባል መስዋዕትነትን እየከፈሉ ላሉ የዘማች ቤተሰቦች ከተማ አስተዳደሩ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ከጎናቸው እንደሚቆም ገልጸዋል።

ታሪኳ መንግሥተአብ