ግንቦት 25/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመድናዋ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት 500 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።
ቤቶቹ የሚገነቡት ፕሮፐርቲ 2020 በተባለ የደቡብ አፍሪካ የቤት አልሚ ካምፓኒ መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቤት አልሚ ካምፓኒ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ካምፓኒው ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በጀት የመደበ ሲሆን፣ የከተማ አስተዳደሩ ለግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ያቀርባል ተብሏል።
በመጀመሪያው ዙር 100 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡም የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል፡