ከተማ አቀፍ የሴቶች የብልፅግና ድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – “ሁሉም ሴቶች ለብልፅግና፤ ብልፅግና ለሁሉም ሴቶች” በሚል ከተማ አቀፍ የሴቶች የብልፅግና ድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው፡፡

በሰልፉ ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመርኃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ሴት ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ለህዝብ ተወካዮችና ለአዲስ አበባ ምክር ቤቶች እጩ የሆኑ የብልጽግና ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ተገኝተዋል።