ከታክስ እዳ ከ36 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

ሐምሌ 26/2014 (ዋልታ) በ2014 በጀት ዓመት ከታክስ ዕዳ 32 ነጥብ 1 ቢሊየን ብ ለመሰብሰብ ታቅዶ 36 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች የተቋሙን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመዋል፡፡

ግብር ከፋዩ ያለበትን የታክስ እዳ የመክፈል ፍላጎት እያደገ መምጣቱ፣ መንግስት ለግብር ከፋዮች እዳቸውን እንዲከፍሉ ማበረታቻ መስጠቱ እና አመራርና ሰራተኛው የታክስ እዳ የመሰብሰብ ስራን በቁርጠኝነት መምራትና መስራት መቻላቸው ለእዳ አሰባሰቡ ውጤታማነት አስተዋፅኦ ያደረጉ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል፡፡

በግምገማው ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ለዚህ መልካም ስራ አፈፃፀም ጉልህ ሚና ላበረከቱ፤ የታክስ እዳቸውን በወቅቱ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች እና ለሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች  ምስጋና ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡