ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ሰመራ ለተጠለሉ ዜጎች ድጋፍ ተደረገ

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ለተጠለሉ ዜጎች ድጋፍ ተደረገ፡፡
ድጋፉን ዓለም ዐቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን ለ9 ሺሕ ዜጎች ነው ያደረገው::

ድጋፉም የስንዴ ዱቄት፣ አተር ክክ፣ የማዕድ ጨው እና የምግብ ዘይትን ያካተተ መሆኑን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል::

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!