ከንቲባዋ ለራስ ቲያትር ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

ሰኔ 25/2014 (ዋልታ) አንጋፋውና በኢትዮጵያ የጥበብ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውና በርካታ አንጋፋ አርቲስቶችን ለሀገሪቱ ያበረከተው የራስ ቲያትር ቤት አዲስ ግንባታ ዛሬ በከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል፡፡

በግንባታ መሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ላይ ታዋቂዎቹ አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎችና በኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ውጣ ውረድ ውስጥ ትልልቅ ዋጋ የከፈሉ አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኪነጥበቡ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመስራት ላይ እንገኛለን ማለታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከንቲባዋ ጥበባችሁን ተጠቅማችሁ ሀገር ግንባታ ላይ ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ላይ በርትታችሁ ስሩ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡