ከንቲባ አዳነች በሴቶችና ህፃናት ላይ አሸባሪው ቡድን የሚደርሰው ጥቃት ታሪክ ይቅር የማይለው ነው አሉ

ታኅሣሥ 10/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በሴቶችና በህፃናት ላይ ያደረሰው ጥቃት ታሪክ ይቅር የማይለውና በደማቋ ኢትዮጵያ የተጋረጠ አደጋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

የሽብር ቡድኑ እያደረሰ ያለውን ጥቃት በፅናት መመከትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ የማይሹ የውጭ ኃይላትን ድል መንሳት ይገባል ብለዋል።

ከንቲባዋ “በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ሰልፍ እየተሳተፉ ነው፡፡