ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 22/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእርቅ፣ የይቅርታ፣ የሰላም እና የወንድማማችነት እሴቶች መገለጫ ለሆነው የኢሬቻ በዓል   እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ከንቲበዋ በሆራ ፊንፊኔ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ለመታደም ወደ ከተማዋ ለመጡ ሁሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢሬቻ መሻገር ነው፡፡ ኢሬቻ ከፈተናዎች በላይ መረማመድ ነው፡፡ ኢሬቻ የድል ብስራት ነው፡፡ ክረምትን በበጋ መተካት ብቻ ሳይሆን ፈተናን በአስደናቂ ድል፣ ችግሮችን በሁሉን አቀፍ መፍትሄ፣ አይቻልምን በመቻል የመሻገር፣ የለውጥ ከፍታ ማሳያ ነው እነደሆነም ገልፀዋል፡፡

የሆራ ፊንፊኔን በዓል በድምቀት እንድናከብር በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ በማጽዳት፣ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ፣ ከተማውን በማስዋብ፣ ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ላይ ለተሳተፉ የከተማችን ነዋሪዎች እና ተቋማትን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁም ብለዋል።