ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወሎ ግንባር ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዕለት ምግብ እና የአይነት ድጋፍ አደረጉ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወሎ ግንባር በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት 100 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዕለት ምግብ እና ሌሎች የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ከንቲባዋ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በወሎ ግንባር በሚገኙ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት እናንተ ለኢትዮጵያ ስትሉ ህይወታችሁን እየሰጣችሁ እና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ እየተፋለማችሁ ስለሆነ ውለታችሁ አለብን፡፡

ሀገር ለማፍረስ የመጣውን አሸባሪውን የሕወሐት ቡድን ለመፋለም ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ገንዘብ ብቻም አይደለም ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ ይዘን የመጣነው ድጋፍ አብረናችሁ መሆናችንን ለማሳየት ነው ያሉት ከንቲባዋ በቀጣይም  ለሰራዊቱ እና ቤተሰቦቻቸው አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡