ከንቲባ አዳነች ኢሬቻን ለማክበር ለመጡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 20/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ለመጡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው “አዲስአበባ የኢሬቻን በዓል ለማክበር የመጡ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች፤ እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ፤ ቆይታችሁ ያማረና የደመቀ እንዲሆን እንመኛለን ” ሲሉ መልዕክት አስተላፈዋል።