ከንቲባ አዳነች ከዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ስትራቴጂካዊ በሆኑ በተቋማዊ ግንባታ፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ስለ ማሻሻል እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዓለም ባንክ በእነዚህ ወሳኝ መስኮች ላይ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡