ከአድዋ ባልተናነሰ ሕዝቡ በአርበኝነት ከዳር ዳር ተነቃንቋል – ቢቂላ ሁሪሣ (ዶ/ር)

                              የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስታባበሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሣ (ዶ/ር)

ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) የአዲስ ወግ አንድ ጉዳይ ውይይት ‹‹የኅልውና ጥሪ እና አገርን የማዳን ርብርብ›› በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም ‹‹ኢትዮጵያን አኔ አንበርክኬ መግዛት አለብኝ ፤ መግዛት ካልቻኩም አፈራርሻት በፍርስራሿ ላይ እኖራለሁ ብሎ ያሰበ ኃይል የከፈተባት ጦርነት ውስጥ ትገኛለች ሲሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስታባበሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሣ (ዶ/ር) በውይይቱ ገልጸዋል።

በዚህ የኅልውና ዘመቻ ላይም ኢትዮጵዊያን አገራቸውን ለመጠበቅ በፍፁም አርበኝነት ስሜት ከዳር ዳር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በዚህም በአሁን ወቅት ኢትዮጵዊያን በአርበኝነት ንቅናቄ ላይ ናቸው። ፈተናው ለሕዝቦች የጋራ እንቅስቃሴ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ብለዋል።

ከአድዋ ወቅት ከነበረው ንቅናቄ ባልተናነሰ መልኩ ሕዝቡ በአርበኘንት ከዳር ዳር ተነቃንቀዋል ያሉት ሚኒስትሩ ይህም የሕዝቦች አርበኝነት ንቅናቄ ሦስት መሠረታዊ ሂደቶች ውስጥ አንደኛው ‹‹አገርህን ለማዳን ዝመት›› ይላል ብለዋል።

ሁለተኛውም ‹‹ጠብቅ›› የሚል መርህ ያለው ሲሆን በዚህም ሕዝቦች እኔ እያለሁ በአከባቢዬ ፈፅሞ ሽብርና ወንጀል ቦታ አይኖረውም በሚል በንቃት አከባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ሚኒስትሩ ሦስተኛው መሠረታዊ ሀሳብ ‹‹ደግፍ›› የሚል ሲሆን፣ የአገር መከላከያ ሠራዊትን በቁስ፣ በገንዘብና በስነልቦና በመደገፍ የአገር ኅልውና ዘመቻውን ከግብ ማድረስና የአገርን ድል ማብሰር ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ለዚህም አገራችንና ሕዝቧ ያልተነካ እምቅ የሆነ አቅም እንዳለው እያሳየ ይገኛል ነው ያሉት ቢቂላ ሁሪሣ (ዶ/ር)፡፡