ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የቆየው ከሰቆጣ ኮረም የሚወስደው መንገድ ድልድይ ጥገና እየተካሄደ ነው

ኅዳር 7/2015 (ዋልታ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ባለው ድጋፍ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የቆየው ከሰቆጣ ኮረም የሚወስደው መንገድ ድልድይ ጥገና ተጀመረ፡፡

ለመንገድ ሥራው ፍጥነትና ስኬት በቀጣናው የሚገኘው ዕዝ የመሃንዲስ መምሪያ የዶዘር፣ ሎደርና የጥበቃ ድጋፍ በማድረግ ለመንገድ ጥገናው አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

የተገኘውን ሰላም ተጠቅሞ ህብረተሠቡ በተረጋጋ ሁኔታ ፊቱን ወደ መሠረተ ልማት እያዞረ መሆኑን የዛታ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ለሀገር ክብር የቆመው መከላከያ ሠራዊት አሰተማማኝ ሰላም እንዲኖር የሚያደርጋቸው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴዎች እና የተቋረጡ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የሚያከናውናቸው ተግባራትንም የአከባቢው ህብረተሰብ አድንቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተወካይ ዋሚድ ዳባ በበኩላቸው የፈረሰው የጥራሪ ድልድይ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በፍጥነትና በአስተማማኝ ሁኔታ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለመንገድ ሥራው ፍጥነትና ስኬት በቀጣናው የሚገኘው ዕዝ የመሃንዲስ መምሪያ ላበረከተው አስተዋፅኦም ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW