ከአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ውይይት

መስከረም 21/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦባሳንጆ ጋር ተወያዩ።
ፕሬዝዳንቷ “ሰላማዊ መፍትሔን ማምጣት የሚያውቁበት ሰው” ካሏቸው መልዕክተኛ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን በቲውተር ገፃቸው ጽፈዋል።
የናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የዛሬ ወር ገደማ ነበር በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው የተሾሙት።
በተያያዘ ዜና ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጽሕፈት ቤታቸው አማካኝነት አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በፈጸመው ወረራ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 650 ሺሕ ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።